የሆሳዕና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የEducation Management System(EMS) አፕሊኬሽን በይፋ ለማስጀመር ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር የስምምነት ውል ተፈራረመ!
የሆሳዕና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የትምህርት አሰጣጡንና አደረጃጀቱን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ለማበልፀግ ያስቻለውን የትምህርት ማኔጅመንት ሲስተም (EMS) ትግበራ በይፋ ያስጀመረ ሲሆን፣ ከአገልግሎት አቅራቢው ኢትዮ ቴሌኮም ጋርም የስምምነት ውል ተፈራርሟል።
የሲስተሙ ዋና ዋና ጥቅሞች፡
- ለተማሪዎች፡ የትምህርት ምዝገባን፣ የውጤት መመልከቻን እና የትምህርት መረጃዎችን በኦንላይን በቀላሉ ማግኘት ያስችላል።
- ለአስተማሪዎች፡ የውጤት መመዝገቢያን፣ የተማሪዎችን ክትትል እና የኮርስ አስተዳደርን ያቀላጥፋል።
- ለአስተዳደር፡ አጠቃላይ የትምህርት ሂደቱን ዘመናዊ፣ ፈጣን እና ግልጽ በሆነ መንገድ ለመምራት ይረዳል።
ኮሌጃችን የተጣለበትን የጤና ባለሙያዎችን የማሰልጠን ከፍተኛ ሀላፊነት በላቀ ደረጃ ለመወጣት ቴክኖሎጂን መሰረት ያደረጉ አሰራሮችን መተግበሩን አጠናክሮ ይቀጥላል።
እንኳን ደስ አለን!


